Entries by massk

የስነምግባር ሳጥኖች በኤስድሮስ

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የተገልጋዮችን ቅሬታ እና አስተያየት ለማወቅ የስነ-ምግባር ሳጥኖች በሁሉም ቅርንጫፎች በማስቀመጥ አስተያየቶችን እየሰበሰበ ይገኛል፡፡ የስነ ምግባር ሳጥኖቹ ማንኛውም ትክክል ያልሆነ የስነ-ምግባር ግድፈት፣ ህገወጥ ወይም የሚያጠራጥር እንቅስቃሴ እና ጠባይ በአክስዮን ማህበሩ ክንውኖች በሰራተኞች ፣ በተማሪዎች ፣በወላጆች እና በአቅራቢያ በሚገኙ አጋር ድርጅቶች የስራ ሂደት ላይ ሲታይ አስተያየት ለማድረግ እና ሁላችንም ልጆቻችን በስነምግባር […]

የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን፣ ሳይንስ ላብራቶሪ ቴክኒሺያን እና ጸሐፊ I

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ በርካታ አላማዎችን የያዘ አክሲዮን ማኅበር ሲሆን በአሁኑ ወቅት የትምህርት ሥራ ላይ ትኩረት በማድረግ የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶችን እያስተዳደር ያለ አክሲዮን ማኅበር ነው፡፡ አክሲዮን ማኅበሩ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ መስፈርቱን የሚያሟሉና ብቁ የሆኑ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የሥራ መደቡ የትምህርት መስክ የሥራ ልምድ
1 የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን በሒሳብ፣ በባዬሎጂ፣ በኬሚስትሪ፣ በጂኦግራፊ፣ በታሪክ፣ በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ፣ አይሲቲ፣ስፖክን እንግሊዝ፣ስፖርት፣ግብረገብ እና በሲቪክስ የትምህርት መስኮች የመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ/ች 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሰራ/የሰራች
2 ሳይንስ ላብራቶሪ ቴክኒሺያን በኬሚስትሪ፣በባዬሎጂ እና በፊዚክስ ላብራቶሪ ቴክኒሺያን ዲፕሎማ/ዲግሪ የተመረቀ/ች 4/2 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሰራ/የሰራች
3 ጸሐፊ I ዲፕሎማ በሴክሬተሪያል ሳይንስ ወይም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ

የሥራ ቦታ፡-  አዲስ አበባ

ደመወዝ፡-    በስምምነት

የስራ መደቦች በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች ሲሆን ለተዘረዘሩት ክፍት የሥራ መደቦች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቶች የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በአክሲዮን ማኅበሩ የሰው ሀብትና አስተዳደር ቢሮ በአካል በመቅረብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

አድራሻ፡- ሰንጋ ተራ ሕብረት ባንክ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የአክሲዮን ማኅበሩ ቢሮ

ለበለጠ መረጃ:- 0964 57 27 77

እንኳን ደስ ያላችሁ

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የለቡ ቅርንጫፍ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ክላስተር ማዕከል ስር ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ጋር በተደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር የሚከተለውን ውጤት ማስመዝገብና ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡

የስብሰባ ጥሪ : ለኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር የባለአክሲዮኖች 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 7ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሑድ ታሕሳስ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ግሎባል ሆቴል ይካሔዳል፡፡