Entries by Manager Esdros

የሰሚት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፈጠራ ሥራ ውድድር ጥሩ ውጤት አስመዘገበ

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በጥያቄና መልስ ውድድር እና በፈጠራ ሥራዎች በሚወዳደሩባቸው የተለያዩ መድረኮች ላይ ጥሩ ተፎካካሪ በመሆን ውጤት ማስመዝገባቸው የተለመደ ተግባራቸው ሆኗል፡፡ በዚህም ቀጥሎ የሰሚት ሁለተኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ጋር በተደረገ የፈጠራ ሥራ ውድድር 3ኛ እና 4ኛ ደረጃን በመያዝ የሠርተፍኬት እና የዋንጫ […]

እንኳን የጌታችንን ህመም፣ሥቃይ እና መከራ ለምናስብበት ሁላችን በጉጉት ለምንጠብቀው ሰሙነ ሕማማት በሰላም አደረሳችሁ።

እንኳን የጌታችንን ህመም፣ሥቃይ እና መከራ ለምናስብበት ሁላችን በጉጉት ለምንጠብቀው ሰሙነ ሕማማት በሰላም አደረሳችሁ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር እና ይቅርታን ያሳየበት ታላቅ ውለታውንእያሰብን ምህረት እና በረከት የምናገኝበት ሳምንት ያድርግልን፡፡

ተማሪዎች በህግ ጥላ ስር የሚገኙ ወገኖችን ጎበኙ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የሲኤምሲ የመጀመሪያ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የሰንበት ቁርስ መርሃግብሩን ቀጥሎ በለሚ ኩራ ፖሊስ መምሪያ በህግ ጥላ ስር የሚገኙ ወገኖችን የመጎብኘት እና ቁርስ የማብለት ስራ አከናውኗል፡፡ በመርሃግብሩ ላይ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጆች፣ የትራንስፖርት ሰጪ ተወካዮች እና የትምህርት ቤቱ የአስተዳደር ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡ በዕለቱ ተማሪዎቹ በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ ወገኖች ምግቡን እራሳቸው በማቅረብ እና ቀርበው […]

በመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት የስራ ክንውን ላይ ውይይት ተካሄደ

በአቡነ ጎርጎርዮስ አዋሬ አንደኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት አጠቃላይ የስራ ክንውን እና የሁለተኛ መንፈቅ አመት የስራ አቅጣጫ ላይ ከወላጆች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡ ውይይቱ የመማር ማስተማር ሂደት፣ የተማሪ የትምህርት አቀባበል፣ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት የተማሪዎች ውጤት ላይ አትኩሮ የተካሄደ ነው፡፡ በውይይት መድረኩ በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ያሉ ጠንካራ ጎኖች እና ክፍተቶች በስፋት ተዳሰዋል፡፡ በዚህም […]

ስርቆትን የሚጠየፍ ትውልድ እናፍራ

ስርቆትን የሚጠየፍ ትውልድ እናፍራ!!! ******************* ሰዎች ራሳቸውን የሚያኖሩበት የሚንከባከቡበት እና የሚያሳድጉበት ሀብትና ንብረት ማፍራት ይፈልጋሉ፡፡ ስርቆት ደግሞ ሀብትና ንብረት ለማፍራት የሚደረገውን ጥረት የሚቃረን ወይም የሚያመክን ነው፡፡ የራስ ያልሆነውን ወይም የሌላውን ሰው ሀብት፣ ንብረት ፣ ጥቅም ወይም እሴት ሕገ ወጥና ድብቅ በሆነ መንገድ የራስ ማድረግ ኢግብረገባዊ ድርጊት ነው ሲል የአቡነ ጎርጎርዮስ የ11ኛ ክፍል የግብረገብ ትምህርት መማሪያ […]

የትምህርት አውደ ርዕዩ በስኬት እንደተጠናቀቀ ተገለጸ

በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተዘጋጅቶ የነበረው የትምህርት አውደ ርዕይ በሁሉም ዘርፍ ስኬታማ ሆኖ እንደተጠናቀቀ ተገለጸ፡፡ የአውደ ርዕዩን በስኬት መጠናቀቅ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ም/ዋና ስራ አስኪያጅ (በትምህርት ዘርፍ) አቶ ዘሪሁን ክብረት የገለጹ ሲሆን ስኬታማነቱ የተቀመጠለትን አላማ ያሳካ መሆኑ ነው ብለዋል፡፡ ትልቁ ነገር የተማሪዎቹን ተሰጥኦ በሁሉም ረገድ ይዞ […]

ለሁለት ቀናት የቆየው አውደ ርዕይ በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የተዘጋጀው የትምህርት አውደ ርዕይ የቦርድ ሰበሳቢ እና አባላት፣ የዋናው መስሪያ ቤት የስራ ኃላፊዎች፣ ወላጆች እና ተጋበዥ እንግዶች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በደማቅ የመዝጊያ መርሃግብር ተጠናቀቀ፡፡ በመዝጊያው መርሃግብር በዳኞች የተመረጡ የተማሪዎች የፈጠራ ስራዎች፣ ሥነ-ጥበብ እና ሥነ-ፅሁፍ እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ውጤቶች ከየቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶቹ በመድረኩ ላይ ቀርበዋል፡፡ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የቦርድ […]

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የትምህርት አውደ ርዕይ ተከፈተ

በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለሁለት ቀናት የሚቆየው ታላቅ የትምህርት አውደ ርዕይ ዛሬ መጋቢት 17/2014ዓ.ም በወይራ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በታላቅ ድምቀት ተከፈተ፡፡ የመክፈቻው መርሃግብር የአክስዮን ማህበሩ የቦርድ አባላት፣ የዋና መስሪያ ቤት የስራ ኃላፊዎች፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ የድርጅቱ ሰራተኞች እና የአውደ ርዕዩ አቅራቢ የሆኑ ትምህርት ቤቶች በተገኙበት ተጀምሯል፡፡ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና […]

በባህርዳር ቅርንጫፍ ውይይት ተካሄደ

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የቦርድ ሰብሳቢ እና አባላት እንዲሁም የዋናው መስሪያ ቤት የስራ ኃላፊዎች በባህርዳር አቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ት/ቤት በመገኘት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ፡፡ ውይይቱ ከተደረገባቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል አንዱ ከማኅበረ ቅዱሳን ባህርዳር ማዕከል ጋር በጅምር በቆዩ ስራዎች እና ወደፊትም አብሮ ከመስራት አንጻር የተደረገ ስብሰባ ሲሆን የማኅበረ ቅዱሳን ባህርዳር ማዕከል ሰብሳቢ፣ምክትል […]

አክስዮን ማህበሩ ለዋና መስሪያ ቤት አመራሮች ስልጠና ሰጠ

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አክስዮን ማህበር ለዋና መስሪያ ቤት አመራሮች እና ቡድን መሪዎች በስልታዊ አመራር ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡ በስልጠናው ቅን መሪ መሆን ፣ ውሳኔ ሰጭነት፣ ድርጅታዊ አቅም ፣ የአመራር ደረጃዎች፣ በራዕይ መምራት እና ጥልቅ እሳቤ የመሳሰሉት ርዕሰ ጉዳዮች በስፋት ተዳሰዋል፡፡ ውጤታማ መሪ ቅንነት እና አቅም ሲመጣጠኑ የሚመጣ ነው ያሉት በዕለቱ ስልጠናውን የሰጡት አቶ ትዛዙ […]