Entries by Manager Esdros

ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ የመንፈሳዊ ጉዞ መርሃግብር አካሄደ

በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የአቡነ ጎርጎርዮስ ሲኤምሲ የመጀመሪያ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ወደ ገዋሳ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ወአቡነ ሀብተማርያም ገዳም መንፈሳዊ ጉዞ በማድረግ የተለያዩ መርሃግብሮችን አካሄደ፡፡ የወላጅ ተማሪ መምህራን ህብረት(ወተመህ) የትምህርት ቤት ሥነ-ምግባር ዘርፍ ባዘጋጀው በዚህ መርሃግብር ላይ ወላጆች፣መምህራን፣ የዋና መስሪያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣ የትምህርት ቤቱ የተማሪዎች የፓርላማ አባላት እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶችም […]

የሀዘን መግለጫ

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የስራ ኃላፊዎች ፣ሰራተኛው እና መላው የድርጅቱ ማህበረሰብ የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አራተኛ ፓትርያሪክ ብፅእ አቡነ መርቆሪዎስ ከዚህ አለም እረፍት ድካም በማለፋቸው ሀዘን ተሰምቶናል! ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን እንመኛለን!

ውሸት

ሰው ሰብአዊ ፍጡር ሆኖ መኖርና ማደግ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያለ ግብረገብ  የኖረበት ጊዜ የለም ፡፡ ይህ ማለት ለሰው ህይወት የሚበጅ የግብረገብ መሰረታዊ መርህ ፍለጋ ከጥንት ጀምሮ ነበረ፡፡ ፍለጋው ዛሬም ቢሆን ቀጥሏል፡፡ ምክንያቱም ብዙ የተባሉ ነገሮች  ቢኖሩም  ሁሉኑም የሚያስማማ መርህ ዛሬም የተገኘ አይመስልም፡፡ እውነተኛ ችግሩ ግን ሁሉኑም የሚያስማማ መርህ መታጣት አይደለም፡፡ ይልቁንም ሰው በተፈለገው መንገድ ራሱን […]

የፈጠራ ስራዎች ለዕይታ ቀረቡ

ተማሪ ስምኦን ደረጄ የ11ኛ ክፍል ተማሪ በርካታ የፈጠራ ስራዎችን መስራት የቻለ ታዳጊ ሲሆን የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ የተማሪዎቹን የፈጠራ ስራዎች ለወላጅ ፣ ለመምህራን  እና ለተማሪዎች ባሳየበት መድረክ ላይ ስራዎቹን ለዕይታ ካቀረቡት ተማሪዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ በዕለቱ ልክ እንደ ስምኦን በተለያዩ ተማሪዎች የተፈጠሩ  በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰሩ ድረ ገጾችን፣ ችግር ፈቺ […]

በልጆች አስተዳደግ ዙሪያ ለወላጆች እና አሳዳጊዎች ስልጠና ተሰጠ

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወይራ ቅርንጫፍ በልጆች አስተዳደግ እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለወላጆች እና አሳዳጊዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡ ስልጠናው ወላጆች/አሳዳጊዎች ስለልጆቻቸው ማወቅ ስለሚኖርባቸው ዋና ዋና ነገሮች ላይ እንዲሁም ልምዶቻቸውን  እንዴት ለልጆቻቸው ማካፈል እንደሚኖርባቸው ብሎም ልጆች በእድሜያቸው የሚያጋጥማቸውን  የተለያዩ ተግዳሮቶች እንዲቋቋሙ ምን ማድረግ እንደሚኖርባቸው እና ተጨማሪ በልጆች አስተዳደግ ዙሪያ ያሉ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ልጆች […]

በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል የልምድ ልውውጥ ተካሄደ

በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስሪ አ.ማ በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች መካከል በአዋሬ ቅርንጫፍ ት/ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ ተካሄደ፡፡ የሁሉም ቅርንጫፍ ት/ቤቶች ርዕሰ መምህራን በተገኙበት የተካሄደው ይህ የልምድ ልውውጥ አጠቃላይ የመማር ማስተማር ሂደትን  በተመለከተ የተሻለ አፈጻጸም ያለው ቅርንጫፍ ት/ቤት  ለሌሎች ቅርንጫፍ ት/ቤቶች ተሞክሮውን የሚያካፍልበት ነው፡፡ የልምድ ልውውጡ አዘጋጅ ቅርንጫፍ ት/ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ደረጄ በቀለ በቅርንጫፍ […]

ት/ቤቶቹ በውድድር መድረኮች ማሸነፋቸውን ቀጥለዋል

የአቡነጎርጎርዮስ ት/ቤቶች በጥያቄና መልስ የውድድር መድረኮች ላይ ብልጫ ማስመዝገባቸውን ቀጥለዋል፡፡ የአቧሬ ቅርንጫፍ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ከሚገኙ ት/ቤቶች ጋር በተካሔደ የ 8ኛ እና 4ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድር አሸናፊ ሆነ፡፡ የጥያቄና መልስ ውድድሩ የቀለም ትምህርቶች ላይ ያተኮረ ሲሆን በ8ኛ ክፍል ውድድር ላይ 2 ተወዳዳሪዎች ተሳትፈው 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡ […]

የወላጅ እና መምህራን የገጽ ለገጽ ውይይት ተካሄደ

በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች የወላጅ እና መምህራን የገጽ ለገጽ ውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡ በመድረኩ የአንደኛ መንፈቅ ዓመት አጋማሽ ፈተና ውጤት፣ የተማሪዎች ባህሪ፣ ከተማሪዎች ወላጅ ጋር ስላለው ግንኙነት እንዲሁም ተማሪዎች ከመመህራን ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን መምሰል እንደሚኖርበት ውይይት ተካሂዷል፡፡ ይህ ባሳለፍነው እሁድ ተከብሮ ያለፈው ሁለተኛው የወላጅ እና መምህራን የገጽ ለገጽ ውይይት ቀን […]

ሰው አክባሪ ትውልድ እናፍራ!!!

ግብረገብነት እያንዳንዱ ሰው ከሌሎች ሰዎች እና ከራሱ ሕይወትና እድገት፣ መብትና ነፃነት፣ ጥቅምና ፍላጎት፣ ክብርና ዓላማ አንፃር ማድረግ የሚገባው ወይም ማድረግ የማይገባው ድርጊት መሆን የሚገባው ጠባይ ወይም መሆን የማይገባው ጠባይ ነው ሲል የአቡነ ጎርጎሪዮስ ት/ቤቶች የግብረገብ ትምህርት መማሪያ መፅሀፍ ይገልፃል፡፡ ታዲያ ግብረገብነት መገለጫዎቹ በርካታ ኢትዮጵዊ እሴትን የያዙ ድርጊቶች ሲሆኑ ከነዚህ መሀከል አንዱ ሰው አክባሪነት ነው፡፡ ሰው […]

የአቡነ ጎርጎርዮስ ወይራ ቅርንጫፍ ት/ቤት በጥያቄና መልስ ውደድር ጥሩ ውጤት አስመዘገበ

የአቡነ ጎርጎርዮሰ ትምህርት ቤቶች ወይራ ቅርንጫፍ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ4ኛ እና 8ኛ ክፍል ጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ተሳትፎ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ፡፡ የጥያቄና መልስ ውድድሩ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አዲስ ህይወት ክላስተር ውስጥ ከሚገኙ 10 ትምህርት ቤቶች ጋር የተደረገ ነው፡፡ በውድድሩ ላይ ሁለት ተማሪዎች የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች ወይራ ቅንጫፍ የመጀመሪያ ደረጃ […]