Entries by Manager Esdros

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ለ አመራር አካላት፣ ለርዕሳነ መምህራን እና ለዕቅድ ዝግጅት ኮሚቴ አባላት በዕቅድ ዝግጅት ሂደት ላይ ሥልጠና ሰጠ፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ለከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮቹ እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ዝግጅት ላይ ለሚሳተፉ የ ዕቅድ ዝግጅት ኮሚቴ አባላት አጠቃላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናው የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የ2017 የበጀት እቅድ ወጥና ተመሳሳይ አካሄድ እንዲኖር ከቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች እስከ ዋናው መሥሪያ ቤት ተመጋጋቢና የተናበበ፣ የሚመዘን፣ ሊደረስበት የሚችል ውጤታማ የሆነ እና […]

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና እንዱስትሪ አ.ማ በድሬደዋ አቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የሚሰጠውን አገልግሎት እንደሚያሳድግ አስታወቀ

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና እንዱስትሪ አ.ማ በድሬደዋ አቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ያለውን የመማር ማስተማር ሥራ የበለጠ ውጤታማ፣ ጥራቱን የጠበቀ እና አሁን ያለውን ሰፊ ፍላጎት ሊያሟላ የሚያስችለውን ተጨማሪ ክፍሎች ያሉት ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ቤት እንደሚከፍት አስታወቀ፡፡ ኩባንያችን ካሉት 27 የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ድሬደዋ ቅርንጫፍ አንዱ ሲሆን ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ለማስፋፈት በ5034 ካሬ ሜትር […]

4ኛው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የፈጠራ ሥራና ዐውደ ርእይ በታላቅ ድምቀት ተከፈተ!

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የትምህርት ዐውደ ርእይ እና የፈጠራ ሥራዎች ውድድር መርሀግብር ከዛሬ አርብ መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ እሁድ መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል፡፡ በዚሁ ለ4ኛ ጊዜ በሚካሄደው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በኪነጥበብ፣ የተማሪ የፈጠራ ሥራ፣ ICT፣ ሥዕልና ቅርጻቅርጽ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኙት 18 የአቡነ ጎርጎርዮስ […]

ኤስድሮስ ሪል እስቴት የመጀመሪያውን ምዕራፍ አጠናቀቀ

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ አካል የሆነው ኤስድሮስ ሪል እስቴት 22 አካባቢ እያስገነባ የሚገኘውን ባለ 3B+G+15 ግንባታ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነው የእስትራክቸር ሥራ ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የግንባታና ምህንድና ዘርፍ እንዳስታወቀው የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነው የእስትራክቸር ስራ ማጠናቀቁና በቀጣይም የህንጻውን የማጠናቀቂያ ስራዎች ለመስራት ዝግጅት መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ባማኮን ኮንስትራክሽን በዋና ኮንትራክተርነት እና ሳይ […]

4ኛው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የፈጠራ ሥራና ዐውደ ርእይ ሊከፈት ነው!

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የትምህርት ዐውደ ርእይ እና የፈጠራ ሥራዎች ውድድር መርሀግብር አርብ መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ይከፈታል፡፡ ለ4ኛ ጊዜ በሚካሄደው የትምህርት ዐውደ ርእይ እና የተማሪዎች የፈጠራ ሥራ በኪነጥበብ፣ የተማሪ የፈጠራ ሥራ፣ ICT፣ ሥዕልና ቅርጻቅርጽ፣ የተቋሙ እሴት እና ዲኮረሽን (የተሰጠህን ቦታ ማሸብረቅና ማስዋብን) ዘርፍ ላይ ውድድር የሚካሄድበት ሲሆን ከመጋቢት 20 እስከ 22 ቀን […]

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ በልዩ ቅናሽ አክሲዮን ለሽያጭ አቀረበ

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ በበርካታ አዳዲስ የኩባንያችን ባለአክሲዮን ለመሆን ፍላጎት ባላቸው ደንበኞቹ ጥያቄ መሰረት እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ብቻ የሚቆይ አዳዲስ አክሲዮኖችን እንደሚሸጥ ነው ያስታወቀው፡፡ ዘመኑን በዋጁ 12 ባለ አክሲዮኖች በብር 100 ሺህ ተመስርቶ በአሁኑ ወቅት ከ3750 በላይ ባለ አክሲዮኖች ያቀፈው ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ አዳዲስ አክስዮኖችን በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ […]

ዝቅተኛ የአክሲዮን መሸጫ

ከዚህ ቀደም መግዛት የሚቻለው ዝቅተኛው የአክሲዮን መጠን 100 አክሲዮን የነበረው በደንበኞቻችን ጥያቄ መሰረት 50 አክሲዮን እንዲሆን ተደርጓል ፡፡  

የሥራ አመራርና አስተዳደር ስልጠና ተሰጠ፡፡

በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን፣ ለፈረቃ አስተባባሪዎች እና ለክፍል ኃላፊዎች በሥራ አመራርና አስተዳደር ርዕሰ ጉዳዮቸ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የስልጠናው ዓላማ የትምህርቱን አስተዳደር የሚመሩ አካላት በአስተዳዳር ሥራ ላይ የሚገጥማቸውን ችግሮች መፍታት በሚያስችላቸው ክህሎት ላይ ውጤታማ በማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱን ማቀላጠፍ የሚያስችል ተተኪዎችን ለማፍራት ያለመ እንደነበር ታውቋል፡፡ ስልጠናው በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና […]

ሰሚት ቅርንጫፍ ከሞዴል አፍሪካ ሽልማት ተበረከተለት ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሞዴል አፍሪካ ኢትዮጵያ አዘጋጅነት አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከሚገኙ 4 ትምህርት ቤቶች ጋር አፍሪካዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በተደረገ የቃል ክርክር/ debate/ ላይ በመሳተፍ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በተዘጋጀ “የ21ኛው ክፍለ ዘመን የአፍሪካ የልማት አቅጣጫ የወጣቶች ግብ በ2030” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ የክርክር መድረክ […]

ለመምህራን ሥርዓተ ትምህርት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጠ፡፡

በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች መምህራን ሥርዓተ ትምህርቱን ውጤታማ ማድረግ በሚያስችሉ ርዕስ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ የስልጠናው ዓላማ መምህራን ሥርዓተ ትምህርቱን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ተገቢ ክህሎት እንዲኖራቸውና የተቃና አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል ሲሆን ቁጥራቸው 86 የሚደርሱ መምህራን የተሳተፉበት በ5 ርዕሳን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥተዋል፡፡ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና […]