Abune gorgorios

በ2015 ዓ.ም በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተዘጋጀ የዕውቅና እና ሽልማት መርሐ-ግብር ላይ በ2015 ዓ.ም ሚኒስትሪ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡
በዚሁ መርሐ-ግብር ላይ በ2015 ዓ.ም ተማሪ ባሮክ ቴዎድሮስ 99.99%፣ ተማሪ አቤሜሌክ መለሰ 99.98% እና ተማሪ መክሊት ሰለሞን 99.98% ከ6ኛ ክፍል እንዲሁም ሰበነማርያም ዳንኤል ከ8ኛ ክፍል 99.97% ውጤት በማስመዝገብ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ተማሪዎቹ ሽልማት የተበረከተላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 30ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባዔ በማጠናቀቂያ መርሐ-ግብር ላይ ዓመቱን በስኬት ላጠናቀቁ አካላት ዕውቅና ለመስጠት በተዘጋጀ መድረክ ላይ መሆኑን ከከተማው አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በመረሐ ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የዕውቅና ሥነ-ሥርዓቱ በተማሪዎች መካከል ጤናማ ፉክክር የሚፈጥር መሆኑን ገልፀው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የነገ የኢትዮጵያ ተስፋ ለሆኑ ተማሪዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አቧሬ ቅርንጫፍ ተማሪ የሆኑት ተማሪ ባሮክ ቴዎድሮስ እና ተማሪ አቤሜሌክ መለሰ፣ ከሲኤምሲ ቅርንጫፍ ተማሪ ሰበነማርያም ዳንኤል እና ተማሪ መክሊት ሰለሞን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ከዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እጅ የታብሌት እና ሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቶላቿዋል፡፡

የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

Esdros construction

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ለአዳዲስ ሠራተኞች ሥልጠና ሰጠ፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ኮርፖሬት የሰው ሀብት አስተዳደር 84 አዳዲስ ሠራተኞች በግሎባል ሆቴል ነሐሴ 17 እና 18 ቀን 2015 ዓ.ም Induction and Socialization ፕሮግራም ያካሄደ ሲሆን በዚህም በ Organizational Awareness and Specific Orientation, Generic Competency for Effective Service Delivery and Esdros’ Rules and Regulations በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ለሁለት ቀናት በተዘጋጀው በዚሁ ስልጠና ላይ የተሳተፉት በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሥራ የሚጀምረው አቡነ ጎርጎርዮስ ሰንሻይን ቅርንጫፍ መምህራን እና ድጋፍ ሰጪ አካላት ሲሆኑ ስልጠናው የተቋሙን እሴት፣ ግብና አጠቃላይ ሁኔታ በመረዳት ሥራቸውን በቀላሉ እንዲያከናውኑ እንዲሁም በስራ ድርሻቸው ምን እንደሚጠበቅባቸው እውቀት እንዲኖራቸው ያለመ እንደነበር ታውቋል፡፡

የስልጠናውን መጀመር በንግግር የከፈቱት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ምክትል ሥራ አስኪያጅና የትምህርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ክብረት “እንኳን ደህና መጣቹሁ!” በማለት ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን ሰልጣኞች የኩባንያውን አጠቃለይ ባሕርይ በመረዳት በቀጣይ በሥራ ሂደት ሊያውቋቸውና ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ ዐበይት ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡ ስልጠናው ኤስድሮስን ይበልጥ የሚያውቁበት እንደሚሆንና የመማር ማስተማሩን ተግባር ለማከናወን የሚያስችል ክህሎትና አስፈላጊ መረጃ የሚያገኙበት እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ስልጠና የወሰዱትን 84 ሰልጣኝ ሠራተኞችን ጨምሮ ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ከ1600 በላይ ሠራተኞች ያሉት መሆኑን ከኤስድሮስ ኮርፖሬት የሰው ሀብት አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Esdros Construction

Esdros construction

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ከአሐዱ ባንክ ጋር ተፈራረመ

በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ እና በአሐዱ ባንክ መካከል የጋራ ሥራ ስምምነት ፊርማ በአሐዱ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ተደረገ፡፡
የመግባቢያው ስምምነት በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ. ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ ፈለቀ እና በአሐዱ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በአቶ ሰፊዓለም ሊበን መካከል ተደርጓል፡፡
በዚህም የመግባቢያ ስምምነት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ቋሚ ሰራተኞች የቤት መግዣና መስሪያ ብድር፣ መኪና መግዣ እንዲሁም ለግል አገልግሎት የሚሆን ብድር ከባንኩ እንዲያገኙ የሚያስችል ይሆናል፡፡
በዚህ በጋራ ለመስራት በተደረገው ስምምነት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ በባንኩ በኩል የባንክ አገልግሎትን እንዲፈጽም ከስምምነት የተደረሰ ሲሆን ባንኩም ለቤት መግዣ ብድር እስከ 25 ዓመት የሚቆይ ብድር እና አንድ አመት የብድር መክፈያ እፎይታ ጊዜን የሰጠ ሲሆን ለቤት መስሪያ ብድር እስከ 25ዓመት የሚቆይ ብድር እና እስከ 2 ዓመት ድረስ የብድር መክፈያ እፎይታ የሚሰጥ መሆኑን በተደረሰው ስምምነት ተካቷል፡፡

ለመንቀሳቀሻ መኪና መግዣ ብድር የተሸከርካሪው የስሪት ዓመት ከ10 ዓመት ያልበለጠ ሆኖ የብድር መክፈያው ጊዜም በ10 ዓመት ውስጥ ተፈጻሚ የሚሆን ብድርም የተካተተበት ነው፡፡ ሠራተኛው ለግል አገልግሎት እስከ 700 ሺህ ብር ብድር መበደር የሚችል ሲሆን የብድሩ መክፈያ የጊዜ ወሰን እስከ 3 ዓመት የሚቆይ መሆኑን ከስምምነት ሰነዱ ያገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከ1600 በላይ ሠራተኞች ያሉት ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የሠራተኛውን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ ባንኮች ጋር ስምምነቶችን በመፈጸም በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል፡፡
የአክሲዮን ማህበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com/e/ በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ።

 

Esdros Share Company

Abune gorgorios

በ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ውጤት የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች 2ኛ ወጣ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ2015ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች በተካሄደው የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ሚኒስትሪ ፈተና ተማሪ ባሮክ ቴዎድሮስ 99.99 ውጤት በማስመዝገብ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች ሁለተኛ ወጥቷል፡፡
ከ28 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ በተዘጋጀው የ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአቧሬ ቅርንጫፍ ተማሪ የሆነው ተማሪ ባሮክ ቴዎድሮስ ከ73,667 መካከል 2ኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡
ሰኔ 28 እና 29 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብቻ በ182 የመፈተኛ ጣቢያዎች በተከናወነው የ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ካሰፈተናቸው 73,667 ተማሪዎች መካከል ተማሪ ባሮክ 2ኛ መሆን ችሏል፡፡
ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ይፋ በተደረገው የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ውጤት ተማሪ ባሮክ ቴዎድሮስ ከአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አቧሬ ቅርንጫፍ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ለፈተና ከቀረቡ አጠቃላይ ተፈታኝ ተማሪዎች መካከል 99.99 ያስመዘገበ ተማሪ በመሆን የ2ኛ ደረጃን ማግኘቱን ከቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

Abune Gorgorious          

Abune gorgorios

የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በሚኒስትሪ ከፍተኛ ውጤት አስመዘገቡ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ2015ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈታኝ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ታሪክ ሠርተዋል፡፡
ሰኔ 26 እና 27 ቀን 2015 ዓ.ም በተሰጠው የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አምስት ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች 625 ተማሪዎችን ማስፈተናቸው ታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ይፋ በተደረገው ውጤት መሠረት በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአዋሬ፣ የለቡ፣ የወይራ፣ የሲኤምሲ እና የቃሊቲ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ካስፈተኗቸው 625 ተማሪዎች ውስጥ አማካይ ውጤታቸው (ጥሬ ማርካቸው) ከ90% በላይ ያመጡት 53 ተማሪዎች፣ከ80-89.9% ያመጡት 183 ተማሪዎች፣ ከ70-79.9% ያመጡ ተማሪዎች 231 ሲሆኑ ቁጥራቸው 158 የሚሆን ተማሪዎች ማለትም 25% የሚሆኑ ተማሪዎች አማካይ ውጤታቸው 70% እና ከዚያ በታች መሆኑን ከኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የትምህርት ዘርፍ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በአሁኑ ወቅት 17ሺህ ተማሪዎችን እያስተማረ የሚገኘው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ2016 ዓ.ም ተቀብሎ የሚያስተምራቸውን የተመሪዎች ቁጥር ከ 18 ሺህ በላይ በማሳደግ አገልግሎቱን ተደራሽ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

 

Abune Gorgorious

 

 

 

 

 

Abune gorgorios

ዝክረ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ተካሄደ

Esdros S.C, [8/1/2023 2:26 PM]
[ Album ]
ዝክረ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ተካሄደ
******************** ******************** ********************
ሐምሌ 22/1982 ዓ.ም በድንገተኛ የመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እረፍት በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ማኔጅመንት እና ሠራተኞች ተዘክሯል፡፡
በታላቁ አባት በብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የእረፍት መታሰቢያ ዝግጅት ላይም ዋኖቻችሁን አስቡ በሚል ኃይለቃል ትምህርተ ወንጌል የተሰጠ ሲሆን የብጹዕነታቸው የሕይወት ታሪክ እና ሥራዎች በሰፊው ተዳሰዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር በዕለቱ የብጹዕነታቸውን ሕይወት ከውልደት እስከ እረፍት የሚያወሳ ሥነ-ጽሑፍ የቀረበ ሲሆን በዚህም በ1932ዓ.ም ከአቶ ገበየሁ እሰየና ከወ/ሮ አሰለፈች ካሣ በስእለት በደሴ ከተማ መወለዳቸው፣ በደሴ መድኃኔዓለም ፊደልን መቁጠር መጀመራቸው፣ በ1963ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት በብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ወደ ግሪክ መላካቸው፣በደሴተ ፍጥሞ ለሁለት ዓመት መንፈሳዊ ትምህርት ተምረው ዲፕሎማ፣ ከአቴንስ ዩኒቨርስቲ በሥነ መለኮት የማስትሬት ዲግሪ፣ ከስዊዘርላንድ ፍሪበሪን ዩኒቨርስቲ በፈረንሳይኛ ቋንቋ የምስክር ወረቀት እንዲሁም በኢየሩሳሌም ደብረ ጽዮን የግሪክ መንፈሳዊ ኮሌጅ- በአረብኛ ቋንቋ የምስክር ወረቀት ማግኘታቸው ተወስቷል፡፡

Esdros S.C, [8/1/2023 2:26 PM]
በመርሐ ግብሩ ላይ ከተወሳው የብጹዕነታቸው ታሪክ አስገራሚው ብጹዕነታቸው በኢየሩሳሌም እያሉ አንድ ቀን ሌሊት ከተኙበት ክፍል አንድ ቀላ ያለ ረጅም ሰው ቀስቅሷቸው አሁን በዚህ የምትቀመጥበት ጊዜ አይደለም፤ ወንጌል ለማስተማር ወደ ኢትዮጵያ እንሂድ ይላቸዋል፡፡ በትእዛዙ ግራ በመጋባት ማንነቱን ሲጠይቁት ኤፍሬም ሶርያዊ ነኝ ይላቸዋል፡፡ ከዛም ጠዋት ከብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ጥሪ ደረሳቸው፡፡ በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም. ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ኤጲስ ቆጶስ ዘሸዋ ተብለው ተሾሙ፡፡
ብጹዕነታቸው ለቅዱስ ሲኖዶስ የመተዳደሪያ ደንብ አዘጋጅተው እንዲጸድቅ ማድረግ የቻሉ ታላቅ ሊቅ ሲሆኑ ለካህናት ማሠልጠኛ ሥርዓተ ትምህርት ቀርጸው፡ የመማሪያና ማስተማሪያ ጥራዝ አዘጋጅተው ያስተምሩ ነበር፡፡ በዝዋይ ሐመረ ብርሃን በመሠረቱት የቅዱስ ገብርኤል ገዳም የዕውቀት ዓምባ አቋቁመው ኢትዮጵያዊውን ታሪክ ከዓለሙ ጋር እያነጻጸሩ ለደቀመዛሙርቶቻቸው ያስተመሩም ነበር። ለገዳማውያኑና ለትምህርት ከየከተማው ለሚሰባሰቡት ተማሪዎቻቸው ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን ለተማሪዎቹ ዕውቀትና ሥነ ልቡና በሚመጥን መልኩ ሲያቀርቡ መስማት ያስደንቅ ነበር። ለትምህርት ወደ ዝዋይ የሚመጣ በበጀት እጥረት አይመለስም ነበር፡፡ በክረምት መኝታ ቤት ሞልቶ በድንኳን እያደሩ የሚማሩ ተማሪዎች ነበሩ፡፡ ብዙዎች ከዝዋይ መለየት አቅቷቸው በዚያው ቀርተዋል፡፡

የሃይማኖትና የታሪክ ጥናትና ምርምራቸውን “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ” እና “የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ” በሚሰኙ መጻሕፍቶቻቸው ቅልብጭ አድርገው አቅርበዋል።
በ1980 ዓ.ም. 12 የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ተቀብለው በክረምት መርሐ ግብር ማስተማር የጀመሩት ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ለዛሬው የወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበራት መስፋፋት መሠረት መጣላቸው በመርሐግብሩ ላይ ተወስቷል፡፡
ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በነበሯቸው 10 የጵጵስና ዓመታት በርካታ ሥራዎችን በመሥራት ለትውልድ መሠረት መጣል የቻሉ አባት እንደሆኑ በመርሐግብሩ ላይ ተወስቷል፡፡
ሐምሌ 22/1982 ዓ.ም በድንገተኛ የመኪና አደጋ በተወለዱ በሃምሳ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ሕይወታቸውን ያጡት ታሪክን እና የወንጌልን ብርሃን በወጣቱ ሕይወት ላይ ለመፈነጠቅ ወደ መቂ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት ሲፋጠኑ መሆኑን ታሪካቸው ያወሳል፡፡
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ በስማቸው በተሰየመው አቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ታሪካቸውን እምነታቸውንና ለሀገርና ለቤተክርስቲያን የነበራቸውን ራእይ ለትውልዱ እያሳወቀ ዘወትር ብጹዕነታቸውን ሲዘክራቸው ይኖራል፡፡
የብፁዕ አባታችን በረከት ይደርብን!
የአክሲዮን ማህበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com/e/ በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ።

 

Abune Gorgorious

በተያያዘ ዜና
የብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ የእረፍት ቀን መታሰሰቢያ ዝግጅት በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተዘጋጅቷል፡፡
በመርሀ ግብሩም ላይ ካህናት አባቶች ፀሎተ ወንጌል እና ማዕጠንተ ዕጣን የተደረሰ ሲሆን በተማሪዎች እና በመምህራን የብፁዕነታቸው ታሪክ ተወስቷል፡፡ የተለያዩ ዝማሬዎች እና መጣጥፎችም ቀርበዋል፡፡
ብፁዕ አባታችን ከሚታወቁባቸው ኃይለ ቃል አንዱ “ዝም ብለህ ስራህን ሥራ” የሚለው መልዕክተ ቃል ሙሉ በሙሉ ተነቦ የመርሀግብሩ ፍፃሜ ሆኗል፡፡
በመርሀግብሩም ላይም የአቧሬ ቅርንጫፍ የክረምት ተማሪዎች ፣መምህራን እና ወላጆች ተገኝተው ተካፍለዋል።

 

Abune Gorgorious

 

 

Abune gorgorios

ሐምሌ 22 ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉበት ቀን ናት፡፡

Esdros S.C, [7/29/2023 11:39 AM]
ሐምሌ 22 ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉበት ቀን ናት፡፡
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ በስማቸው አቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች በማለት በመላ ሀገሪቱ ትምህርት ቤቶችን ከፍቶ በማስተማር ብፁዕነታቸውን ዘወትር ይዘክራቸዋል፡፡
ለዛሬው የብፁዕነታቸውን እረፍት ለመዘከር ሥራዎቻቸውንና ታሪካዊ ንግግሮቻቸውን ለማንሳት ወደናል፡፡
ሐምሌ 22 ቀን 1982 ዓ.ም. ከጠዋቱ አንድሰዓት ተኩል ወደ መቂ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት ሲሄዱ በድንገተኛ የመኪና አደጋ በተወለዱ በሃምሳ ዓመታቸው አርፈዋል፡፡በዕለቱ አብረዋቸው የነበሩት ዲያቆን ጳውሎስ በቀለና የመኪናው አሽከርካሪ ዲያቆን ኤፍሬም ዘውዴም በለጋ ዕድሜያቸው አርፈዋል፡፡
ሐምሌ 22/1982 ዓ.ም በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን ያጡት በ20ኛው መቶ ክ/ዘመን የወንጌልና የታሪክ ብርሃንን በተለይ በወጣቱ ሕይወት ላይ የፈነጠቁት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ (በድሮው የክፍላተ ሀገር አከፋፈል) የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ።
• በጽሑፋቸው፣ በትምህርታቸው እና ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ባላቸው ጽኑዕ ፍቅር ከእምነት ድንበር ባሻገር የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ልቡና ሊገዛ የሚችል ስብዕና የነበራቸው አባት ነበሩ።

Esdros S.C, [7/29/2023 11:40 AM]
ከመንገድ ሲመጡ የመንፈስ ልጆቻቸውን ሳያዩ አያድሩም፣ የት፣ ለምን እንደሄዱና ምን እንደተደረገ ይነግሩአቸዋል፡፡የሚመገቡትም ከተማሪዎች ጋር ነበር፡፡ ከተማሪዎቹ የሚለዩት በጠረጴዛ ነበር፡፡ መነኮሳት በአንድ ክፍል መጽሐፈ መነኮሳት እየተነበበላቸው ሥርዓተ አበውን እየተማሩ ይመገቡ ነበር፡፡ በምግብ ቤቱ ድምጽ ማሰማት ፈጽሞ ክልክል ነበር፡፡ ዘወትር ለደቀ መዛሙርቱ እዚህ በረሃ የወደቅኩት ሰው አፈራለሁ በማለት እንጂ አልጫ ፍትፍት ብፈልግ ከመሐል ከተማ አልወጣም ነበር፡፡ ለትምህርት ጊዜ ስጡ፡፡ የምንኖረው በዓለም ነው፡፡ ገማቾች ጥያቄ ያቀርቡልናል፡፡ ስለዚህ በመማር ብቁ እንሁን፡፡ በማለት በዓላማ መጽናት እንዳለባቸው ያስተምሩ ነበር፡፡
• ብፁዕነታቸው በዓለም መድረክ የቤተ ክርስቲያን መልእክተኛ ነበሩ፡፡ ተመራማሪና ጸሐፊም ነበሩ፡፡
• ሦስት ጃማይካውያንን በዝዋይ አስተምረው ለማዕርገ ቅስና አብቅተዋል፡፡
• ስድስት ሊቃነ ጳጳሳትን ያፈኑም አንደነበር ይነገራል(ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ራብዕ፣ብፁዕ አቡነ መልከ ጸዴቅ ካልእ፣ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ሣልስ፣ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ፣ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እና ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ)
• ለህትመት የበቁ የብፁዕነታቸው መጻሕፍቶች(መሠረተ እምነት- ለሕጻናት ትምህርተ ሃይማኖትን ለማስተማር የተዘጋጀ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ እና ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን )
• ያልታተሙየብፁዕነታቸው መጻሕፍቶች(ሥርዓተ ኖሎት፣ነገረ ሃይማኖት፣ኦርቶዶክሳዊ የስብከት ዘዴ እና ቤተ ክርስቲያንህን እወቅ)
• ሰላም ተዋሕዶ የተሰኘው የመዝሙር ግጥም ደራሲም ናቸው፡፡
የብፁዕነታቸው ዘመን ተሸጋሪ ድንቅ አባባሎች መካከልም
• ስለ እመቤታችን መናገር የምንችለው ስለሰውና ስለ እግዚአብሔር ስናውቅ ብቻ ነው፡፡
• የቤተ ክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ነው፡፡ ፈተና ይበዛበታል፡፡ ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተ ክርስቲያናችሁን አቋም አጠናክሩ፡፡
• ሰው ፍላጎቱን ካላሸነፈ የእግዚአብሔር ሊሆን አይችልም፡፡
• ሥጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ሕይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው፡፡
• ኢትዮጵያ ለእግዚአብሔር የምሥጢር ሀገር ናት፡፡የሚሉት ከንግግሮቻቸው መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የብፁዕነታቸው በረከት ጥርጥር የሌለባት እምነታቸው ትደርብን፡፡
የጽሑፉ ምንጮች፡-
1) ቤተ ቀሲስ ሰሎሞን ወንድሙ ብሎግ
2) ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ የጻፈውን ጽሑፍ አዲስ ጉዳይ መጽሔት እንዳወጣው- ሐምሌ 2ዐዐ6
3) Abune Gorgoreyos 2 አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ (ታላቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ኢትዮጵያዊ)

 

Abune gorgorious

 

Abune gorgorios

የ2015ዓ.ም ተፈታኞች ሲሙሌሽን (ዋናውን የሀገር አቀፍ ፈተና አምሳያ)የሞዴል ፈተናን መጠናቀቅን በማስመልከት የመዝጊያ መርሀ ግብር ላይ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቪርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የኤስድሮስ የቦርድ እና የማኔጅመንት አካላት፣የትምህርት ኤክስፐርቶች እና ርዕሳነ መምህራን በተገኙበት የተዘጋጀውን የማጠቃለያ መርሀግብር የምንቃኝበትን ዝግጅቶችን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል፡፡

የተማሪዎች በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ቆይታ ያበቃው የሲቪክስ ፈተናን መጠናቀቅን ተከትሎ በተዘጋጀ የማጠቃላያ መርሀ ግብር ላይ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስን ጨምሮ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የዳሬክተሮች ቦርድ አባል ኢንጅነር አስማማው አያሌውን ጨምሮ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንተህ ፈለቀ እና የማኔጅመንት አባላት በተዘጋጀው መርሀ ግብር ላይ በተገኙበት የመጠቃለያ መርሀግብር ተደርጓል፡፡
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት፣የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጰስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ተማሪዎቹን አበረታተዋል፡፡ ብፁዕነታቸው” በአባቶች ፈንታ ልጆች ተተኩ ስምሽንም በሄዱበት ቦታ ሁሉ ይጠራሉ የሚለውን በመዝሙር 44፣16 ላይ ያለውን ኃይለ ቃል በማንሳት እናንተ ሀገርና ቤተክርስቲያንን ለማገልገል በትምህርት ዘርፍ የተሰማራቹህ ናችሁ በማለት የተናገሩት ብፁዕነታቸው እናንተ ከዋንኞቹ ኢትዮጵያውያን የዕውቀት እና የጥበብ መሠረት ከሆኑት እንደ ክርስቶስ ሰምራ ከመንፈሳዊነቷ ባሻገር ስለ ማኅበረሰብ ያላት ፍልስፍና ትልቅ እንደነበር እንዲሁም በ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተወለደው ኢትዮጵያዊው የዕውቀት፣የጥበብ እና የትእግስት ባለቤት የቅዱስ ያሬድን ጥበብ አንስተው ህይወቱን እና ጥበቡን ለተማሪዎቹ አጋርተዋል፡፡ “ኢትዮጵያውያን የዕውቀት ሰዎች ናቸው ብሎ ፈላስፋው ሆሜር የመሰከረልን ሰዎች መሆናችን ልናውቅ ይገባል” ብለዋል፡፡
በመርሀ ግብሩም ላይ ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንደስትሪ አ.ማን በመወከል መልእክት ያስተላለፉት በኤስድሮስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በአቶ አንተነህ ፈለቀ ጋባዥነት አቶ ዘርሁን ክብረት በምክትል ሥራ አስፈፃሚ የትምህርት ዘርፍ ኀላፊ ሲሆኑ “በሁሉም የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት በተሟላ ሁኔታ እና ቁጥር ተዘጋጅተናል “ያሉ ሲሆን ለዚህ ሲሙሌሽንተር (ዋናውን የሀገር አቀፍ ፈተና አምሳያ)የሞዴል ፈተናን መርሀ-ግብር መሳካት የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ፣የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጰስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስን አመስግነዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ማጠቃለም የተማሪዎቹ ተወካዮች ባስተላለፉት መልእክት “ቆይታችን በጣም ደስ የሚል ነበር ይህንን ሲሙሌሽንተር (ዋናውን የሀገር አቀፍ ፈተና አምሳያ)የሞዴል ፈተናን ላዘጋጀልን ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ እና ከሀሳብ ዝግጅት ጀምሮ በጀት መድቦ ይህንን እድል ያመቻቸልንን ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንደስትሪ አ.ማን እናመሰግናለን ያሉት የተማሪዎቹ ተወካይ ይህንን መሰል ዝግጅትም ከእኛ በኋላም ለሚመጡት ተማሪዎች እንዲቀጥል የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን ምስል በተማሪዎቹ አቅራቢነት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንደስትሪ አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንተህ ፈለቀ ለብጹፁዕ አቡነ ፊሊጶስ ስጦታ አበርክተውላቸዋል፡፡ብፁዕነታቸውም ተማሪዎቹ ላቀረቡላቸው ስጦታ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን “ይህንን ስጦታ እናንተ ተማሪዎች የእኔ ስጦታ መሆናቹህን የማይበት ነው” ያሉ ሲሆን “ቀጣዩን ፈተና የምትመልሱበትን ዕውቀት እና ጥበቡን እግዚአብሔር ያድላቹህ” በማለት አባታዊ ቡራኬ ሰጥተዋል ፡፡ከማጠቃላያ መርሀ ግብሩ መጠናቀቅ በኋላም ተማሪዎች በካፌ የምሳ መርሀግብር ላይ ተሳትፈው ከየዶርማቸው ሻንጣቸውን በመሸከፍ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገኛኘት ከየመጡበት ቅርንጫፍ ትምህርት ቤታቸው አምርተዋል፡፡ተማሪዎች በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ቆይታ ያበቃው የሲቪክስ ፈተናን መጠናቀቅን ተከትሎ በተዘጋጀ የማጠቃላያ መርሀ ግብር ላይ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስን ጨምሮ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የዳሬክተሮች ቦርድ አባል ኢንጅነር አስማማው አያሌውን ጨምሮ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንተህ ፈለቀ እና የማኔጅመንት አባላት በተዘጋጀው መርሀ ግብር ላይ በተገኙበት የመጠቃለያ መርሀግብር ተደርጓል፡፡
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት፣የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጰስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ተማሪዎቹን አበረታተዋል፡፡ ብፁዕነታቸው” በአባቶች ፈንታ ልጆች ተተኩ ስምሽንም በሄዱበት ቦታ ሁሉ ይጠራሉ የሚለውን በመዝሙር 44፣16 ላይ ያለውን ኃይለ ቃል በማንሳት እናንተ ሀገርና ቤተክርስቲያንን ለማገልገል በትምህርት ዘርፍ የተሰማራቹህ ናችሁ በማለት የተናገሩት ብፁዕነታቸው እናንተ ከዋንኞቹ ኢትዮጵያውያን የዕውቀት እና የጥበብ መሠረት ከሆኑት እንደ ክርስቶስ ሰምራ ከመንፈሳዊነቷ ባሻገር ስለ ማኅበረሰብ ያላት ፍልስፍና ትልቅ እንደነበር እንዲሁም በ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተወለደው ኢትዮጵያዊው የዕውቀት፣የጥበብ እና የትእግስት ባለቤት የቅዱስ ያሬድን ጥበብ አንስተው ህይወቱን እና ጥበቡን ለተማሪዎቹ አጋርተዋል፡፡ “ኢትዮጵያውያን የዕውቀት ሰዎች ናቸው ብሎ ፈላስፋው ሆሜር የመሰከረልን ሰዎች መሆናችን ልናውቅ ይገባል” ብለዋል፡፡
በመርሀ ግብሩም ላይ ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንደስትሪ አ.ማን በመወከል መልእክት ያስተላለፉት በኤስድሮስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በአቶ አንተነህ ፈለቀ ጋባዥነት አቶ ዘርሁን ክብረት በምክትል ሥራ አስፈፃሚ የትምህርት ዘርፍ ኀላፊ ሲሆኑ “በሁሉም የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት በተሟላ ሁኔታ እና ቁጥር ተዘጋጅተናል “ያሉ ሲሆን ለዚህ ሲሙሌሽንተር (ዋናውን የሀገር አቀፍ ፈተና አምሳያ)የሞዴል ፈተናን መርሀ-ግብር መሳካት የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ፣የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጰስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስን አመስግነዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ማጠቃለም የተማሪዎቹ ተወካዮች ባስተላለፉት መልእክት “ቆይታችን በጣም ደስ የሚል ነበር ይህንን ሲሙሌሽንተር (ዋናውን የሀገር አቀፍ ፈተና አምሳያ)የሞዴል ፈተናን ላዘጋጀልን ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ እና ከሀሳብ ዝግጅት ጀምሮ በጀት መድቦ ይህንን እድል ያመቻቸልንን ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንደስትሪ አ.ማን እናመሰግናለን ያሉት የተማሪዎቹ ተወካይ ይህንን መሰል ዝግጅትም ከእኛ በኋላም ለሚመጡት ተማሪዎች እንዲቀጥል የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን ምስል በተማሪዎቹ አቅራቢነት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንደስትሪ አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንተህ ፈለቀ ለብጹፁዕ አቡነ ፊሊጶስ ስጦታ አበርክተውላቸዋል፡፡ብፁዕነታቸውም ተማሪዎቹ ላቀረቡላቸው ስጦታ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን “ይህንን ስጦታ እናንተ ተማሪዎች የእኔ ስጦታ መሆናቹህን የማይበት ነው” ያሉ ሲሆን “ቀጣዩን ፈተና የምትመልሱበትን ዕውቀት እና ጥበቡን እግዚአብሔር ያድላቹህ” በማለት አባታዊ ቡራኬ ሰጥተዋል ፡፡ከማጠቃላያ መርሀ ግብሩ መጠናቀቅ በኋላም ተማሪዎች በካፌ የምሳ መርሀግብር ላይ ተሳትፈው ከየዶርማቸው ሻንጣቸውን በመሸከፍ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገኛኘት ከየመጡበት ቅርንጫፍ ትምህርት ቤታቸው አምርተዋል፡፡

 

Abune Gorgorious

 

 

Abune gorgorios

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የማኔጅመንት አካላት ከዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀምሮ የለቡ፣ሰሚት እና አቧሬ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የ2ኛ ደረጃ ርእሳነ መምህራን ስለ ተማሪዎቻቸው በነበራቸውን ዝግጅት እና ቅድስት ሥላሴ ዩኒቪርሲቲ የነበራቸውን ቆይታ የምንቃኝበት ምእራፍ፡፡

በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነበረውን የሀገር አቀፍ ፈተና አምሳያ(ሲሙሌሽን) የሞዴል ፈተና ሂደት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንደስትሪ አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚን አቶ አንተነህ ፈለቀን ጨምሮ የማኔጅመንት አካላት ከመርሀ ግብሩ ጅማሮ እስከ ማጠቃለያው ድረስ በከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት አስፈላጊውን ሁሉ ሲያደርጉ እንደነበር በቦታው ተመልክተናል ፡፡ የማኔጅመንት አካላት፣የትምህርት ኤክሰፐርት ባለሙያዎች እና የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የለቡ፣ሰሚት እና አቧሬ ቅርንጫፍ ትምህት ቤቶች የ2ኛ ደረጃ ርእሳነ መምህራን በዩኒቨርስቲ ተቀብለው ከማስገባት ጀምሮ በቆዩባቸው ተከታታይ ቀናትም እንደ ወላጅ በመሆን አብረዋቸው ውለው ማደር ከማደሪያ ክፍል ፣የመመገቢያ አዳራሽ ከምግብ ዝግጅት ተማሪዎቹን እስከ መመገብ ድረስ በአብሮነታቸው ቆይተዋል፡፡
በዚህ መርሀግብር የፈተና ሂደቱን የመሩት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንደስትሪ አ.ማ በትምህርት ዘርፍ የፈተና ክፍል ኃላፊ አቶ መኮንን ዋለ እንደገለጹትም “ለሀገር አቀፍ ፈተናው ከስነ-ልቦና አንጻር በቀጣይ በሚደረገው ሀገር አቀፍ ፈተና በዩኒቨርሲቲ ምንም ዓይነት አስቸጋሪ ጉዳይ አይገጥማቸውም በዚህ መርሀ ግብር በቂ ልምድ ያገኙበት በመሆኑ፡፡ ዋናውን ፈተና እንዲመስል ፈተናዎቹን በተለያዩ ኮድ ከማዘጋጅት ጅምሮ ከተለያዩ ዩኒቪርሲቲ በመጡ መምህራን ፈተናዎቹን እንዲፈተኑም ነው የተደረገው” በማለት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡
ከአቀባበል መርሀ ግብሩ ጀምሮ የሰሚት ቅርንጫፍ ተማሪዎችን ከወላጆቻቸው በአደራ ተቀብለው ወደ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቪርሲቲ ይዘው የመጡት የአቡነ ጎርጎሪዮስ ትምህርት ቤቶች የሰሚት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር አቶ ጣሳቸው ጫኔ የነበረውን ሁኔታ ሲገልጹም “ወላጆች ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ድረስ ልጆቻቸውን አምጥተው ሲያስረክቡ በመርሀ ግብሩ በጣም ደስተኛ ናቸው፡፡ በሂደቱም ተማሪዎች አይዲ ከመርሳት ጀምሮ የገጠማቸው አንዳንድ ችግሮች ለቀጣይ ትምህርት እንዲወስዱ የሚያግዛቸው ሲሆን በነበራቸው ቆይታ ግን በጣም ደስተኛ እንደነበሩ የተመለከትኩበት ነው “ብለዋል፡፡
ሌላው የአቡነ ጎርጎሪዮስ ትምህርት ቤቶች 2ኛ ደረጃ ለኑ ቅርንጫፍ ርእሰ መምህር አቶ ፍሬዘር ገድሉ መርሀ ግብሩን በማስመልከት እንደተናገሩት” ተማሪዎች አድሚሽን ካርዳቸውን ይዘው ፈተናቸውን በኮድ የተፈተኑ ሲሆን በዶርም፣በካፌና በግቢው የነበራቸው አጠቃላይ ሁኔታዎች በሙሉ ለዋናው አገር አቀፍ ፈተና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሲገቡ የሚያደርጉትን በሙሉ ያዩት በመሆኑ በቀጣይ የአቡነ ጎርጎሪዮስ ተማሪዎች ምንም አዲስ ነገር አይገጥማቸውም “ በማለት የነበረውን ቆይታ ገልጸዋል፡፡
የአቡነ ጎርጎሪዮስ ትምህርት ቤቶች 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአቧሬ ቅርንጫፍ ርእሰ መምህር ሳሙኤል ይልማ አጠቃላይ የተማሪዎቻቸውን ሁኔታ ሲገልጹም “ ተማሪዎቻችን ሁለንተናዊ ዝግጅት ከተግባር እስከ ሥነልቦና ዝግጅት ማድረጋቸውን ያየንበት ነው፡፡ ለዚህ መርሀ ግብር መሳካትም ከኤስድሮስ የቦርድ አካላት፣የማኔጅመንት እና የትምህርት ኤክሰፐርቶች ያደረጉት ሁለንተናዊ ተግባር በመሆኑ ሊመሰገኑ ይገባል “ በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

 

Abune gorgoriyos

Abune gorgorios

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ከወላጅና ከቤተሰብ ተነጥለው ለሞዴል ፈተና ወደ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቪርሲቲ ገብተው የነበራቸው ቆይታ ምን ይመስል እንደነበር እንቃኛለን፡፡

ከወላጅ እቅፍ ከቤተሰብ ጓዳ ርቆ ማደርም ሆነ መሰንበትን ያልለመዱት የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሀገር አቀፍ ፈተና የዝግጅት ምዕራፍ አካል የሆነውን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መዋል ማደርን እንዲሁም ሞዴል ፈተናዎችን አስተናግደዋል፡፡

ተማሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸው የተቋጠሩላቸውን ደረቅ ምግቦች፣ልብስ፣ ብርድልብስ እና አንሶላ ሸክፈው በተቀመጠላቸው ቀን በዩኒቨርስቲው ቅጥር የተገኙ ሲሆን አንድ ዶርም ለአራት እና ለአምስት በሚጋሩበት ሁኔታ ከተለያዩ ቅርንጫፍ ት/ቤቶች ጋር በማሰባጠር ዶርም ተደልድለዋል፡፡

ካፌ በወረፋ ለቁርስ ለምሳ እንዲሁም ለእራት የዩኒቨርሲቲውን ደውል ጠብቀው የተሰለፉበትን አዲስ ክስተት ያስተናገዱበት እንደነበርም ተማሪዎቹ አጫውተውናል፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች አዲሱን የአኗኗር ሁኔታ ለመልመድ በመቸገር ከራሳቸው ጋር ሲታግሉ ግማሾቹ አዲሱን የአኗኗር ሁኔታ በፍጥነት በመልመድ በርካቶችን ጓደኛ ማድረግ የቻሉበትና በዶርም ውስጥ ተግባብቶ ልደት ማክበር የሚያደርስ ቅርርብ መፍጠር መቻላቸውንም ለመገንዘብ ችለናል፡፡

ብዙዎች ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ስልክ ይዞ መግባት በመከልከሉ በወላጅ ናፍቆት መቸገራቸውን ተመልክተናል፡፡ እንዳንድ ወላጆችም የልጆቻቸውን ድምጽ ባለመስማታቸው እና ዓይናቸውን ባለማየታቸው እንቅልፍ አጥተው ሰንብተው እንደነበር ቢገልጹም ወደፊት የግድ የሚጋፈጡት ሁነት በመሆኑ መለማመዳቸውን በበጎ መልኩ እንዳዩት ገልጸውልናል፡፡

ተማሪዎቹ በዶርም ለፈተና ዝግጅት በጥናት ተጠምደው የሰነበቱ እንዳሉ ሁሉ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ እስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉ ተሰባስበው የጋራ መዝሙር የሚዘምሩ፣ የጋራ ጸሎት የሚጸልዩ እና የተለያዩ ማኅበራዊ መስተጋብሮችን የሚያከናወኑ ተማሪዎችን ለተመለከተ በዩኒቨርሲቲ ተመድበው በመደበኛ ትምህርት የሚማሩ እንጂ ለሞዴል ፈተና ለተወሰኑ ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲ ያቀኑ ተማሪዎች አይመስሉም ነበር፡፡

ተማሪዎቹ በነበራቸው ቆይታ በርካታ አስተማሪ፣ አዝናኝ እና አግራሞትን የፈጠሩ ክስተቶችን በማስተናገዳቸው ለቀጣይ ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት ትልቅ ልምድና ተሞክሮ ያገኙበት እንደነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡

 

Abungorgorios