Abune Gorgorios

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መክፈቻ መርሐግብር፡፡

Abune Gorgorios

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰንሻይን ቅርንጫፍ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መክፈቻ መርሐግብር፡፡

Abune Gorgorios

Abune Gorgorios

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መክፈቻ መርሐግብር፡፡

Abune Gorgorios

Abune Gorgorios

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች 22 ቅርንጫፍ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መክፈቻ መርሐግብር፡፡

Abune Gorgorious

Abune Gorgorios

የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ደማቅ የመክፈቻ መርሐግብር ተካሄደ፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኙ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በደማቅ የመክፈቻ መርሐግብር የ2016 ዓ.ም ትምህርት አስጀመሩ፡፡
መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም ማለዳ ላይ በየትምህርት ቤቶቹ በተዘጋጀው የመክፈቻ መርሐግብር ላይ በካህናት አባቶች ጸሎተ ዕጣን እና ጸሎተ ወንጌል የተጀመረ ሲሆን የተለያዩ ዝግጅቶች ተከናውነዋል፡፡ በመርሐግብሩም የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ መልዕክት ፣የቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር መልዕክት እና የወላጆች ተወካይ መልዕክት የተላለፈ ሲሆን መምህራን እና ተማሪዎች ዝማሬዎችን አቅርበዋል፡፡ በዝግጅቱ ማብቂያም የችቦ ቅብብሎሽ ሥነ-ሥርዓት የተከናወነበት ደማቅ የመክፈቻ መርሐግብር ተካሄዷል፡፡

 

Abune Gorgorios

Abune Gorgorios

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ ተሸለመ!

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ ጳጉሜ 6 ቀን 2015 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በተዘጋጀው የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር በ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ በክፍለ ከተማው የግል ትምህርት ተቋም 100% ተማሪዎችን በማሳለፍ 1ኛ ደረጃ በማምጣት ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
ሰኔ 26 እና 27 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በተሰጠው የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና 120 ተማሪዎችን ያስፈተነው በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የለቡ ቅርንጫፍ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ካሉ ትምህርት ቤቶች መካከል በ8ኛ ክፍል ፈተና የላቀ ውጤት በማስመዝገብ እና 100% ተማሪዎችን በማሳለፍ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

 

Abune GorgoriousAbune Gorgorious

Abune Gorgorious

አቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የማንነት መገለጫው በሆነው ሥነ-ምግባር እና የግእዝ ቋንቋ ከማስተማር ጎን ለጎን ውጤታማ እና በየከተሞቹ ከሚገኙ የመንግሥት እና የግል የትምህርት ተቋማት መካከል በሣይንስ እና በቴክኖሎጂ እንዲሁም በቀለም ትምህርት በሀገር አቀፍ ደረጃ ተጽኖ ፈጣሪ የትምህርት ተቋም መሆን የቻለ የትምህርት ማዕከል ሆኗል፡፡

 

Abune Gorgorious

Abune gorgorios

አዳዲሶቹ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለ2016 ዓ.ም ሥራ ይጀምራሉ፡፡

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰንሻይን ቅርንጫፍ ለ2016 ዓ.ም አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
በቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ለመስጠት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኘው ሰንሻይን ቅርንጫፍ ቁጥራቸው ከ1ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች 26ኛ እና 27ኛ ቅርንጫፍ በመሆን የተከፈተው የሰንሻይን ቅርንጫፍ ለ2016 ዓ.ም ሥራ መጀመር የሚያስችለውን የማስተማር ፍቃድ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ያገኘ በመሆኑ በይፋ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ሥራ መጀመሩ ታውቋል፡፡

abune Gorgorious

Abune gorgorios

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን አስመረቁ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችን በታላቅ ድምቀት አስመረቀ፡፡
ነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ጦር ኃይሎች አካባቢ በሚገኘው መኮንኖች ክበብ አዳራሽ በተከናውነው የምረቃ መርሐግብር ላይ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጰስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ፣የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት ፣የማኔጅመንት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

abune Gorgorious abune Gorgorious

abune Gorgorious