Entries by Manager Esdros

በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች የሥነ-ምግባር ትምህርት ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ጥናትና ምርምር ቀረበ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች እየሰጠ ያለው እና የት/ቤቱ ቁልፍ እሴት የሆነው የሥነ-ምግባር ትምህርት ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ የጥናትና ምርምር ሥራ በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የትምህርት ኤክስፐርቶች ቀርቧል፡፡ ጥቅምት 6/2016 ዓ.ም በኤስድሮስ ኮንስትራክሽ ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ መሰብሰቢያ አዳራሽ የቀረበውን የጥናትና ምርምር መርሐግብር በንግግር የከፈቱት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ትምህርት ዘርፍ አቶ […]

የ2015 ዓ.ም የስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ውጤት ይፋ ሆነ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ከቅድመ-አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የ2015 ዓ.ም የስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ውጤት ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ ሆኗል፡፡ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወይራ ቅርንጫፍ በኤስድሮስ ትምህርት ዘርፍ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጥና ምዘና ክፍል በተዘጋጀው የ2015 ዓ.ም የተቋማት ስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ግኝት ትንተና እና ውጤት ይፋ የማድረግ መርሐግብር ተካሂዷል፡፡ […]

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ 615 ውጤት ተመዘገበ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ ተማሪ የሆነው ናሆም መርሻ በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 615 በማምጣት ከቀዳሚዎች መካከል መሆን ችሏል፡፡ በ2015 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ከወሰዱ 845 ሺህ 188 ተማሪዎች ውስጥ 27 ሺህ (3.2%) ተማሪዎች ብቻ ከ50 በመቶ በላይ በማምጣት የማለፍያ ውጤት ማስመዝገባቸው ይታወሳል፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር […]

ለኤስድሮስ ሥራ አመራር አባላት ሥልጠና ተሰጠ፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ኮርፓሬት የሰው ሀብት አስተዳደር ከኢንፊኒቲ ኮንሰልቲንግ ሶሉሽን ጋር በመተባበር ለሥራ አመራር አባላት የመጪው ጊዜ የአመራር ክህሎት /Leadership Skills For The future/ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ መስከረም 12 እና 13 ቀን 2016 ዓ.ም ላምበረት በሚገኘው ኃይሌ ግራንድ አዲስ አበባ ሆቴል ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የስልጠናውን መጀመር በንግግር የከፈቱት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና […]