Abune Gorgorious

ወላጆች ከመምህራን ጋር ስለ ልጆቻቸው የሚወያዩበት መርሀግብር ተካሄደ፡፡

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በአዲስ አበባ በሚገኙ 18 ቅርንቻፍ ትምህርት ቤቶች ወላጆች ከመምህራን ጋር ስለ ልጆቻቸው አጠቃላይ ጉዳይ የሚመክሩበት መርሀግብር በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ተካሄዷል፡፡
ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ.ም አላማውን በልጆች የትምህርት ውጤት እና በልጆች ስነምግባር እና የትምህርት ቤት አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ያተኮረ በገጽለገጽ ወላጅ ከመምህራን ጋር የሚወያይበት በውይይቱም ጠንካራ ጎን የሚጎለብትበትን እና ትግሮች ደግሞ በጋራ መፍትሄ የሚበጅለትን አላማ ለማሳካት ያለመ ዝግጅት ነበር፡፡

ይህንን መሰል መርሀግብር በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በሁሉም ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የተለመደና ባህል መሆኑ የተገለጸው፡፡ የወላጆችና የመምህራን ገጽለገጽ መርሀግብር በየመንፈቅ ዓመት አጋማሽ ላይ የሚደረግ በመሆኑ ተማሪዎች መንፈቅ ዓመቱን ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ የወላጅ እና የመምህራን የጋራ ድጋፍን ከመፍጠሩም በላይ የክፍተት ቦታዎችን መሙላት ያስችላል፡፡
ዕለተ እሁድ ታህሳስ 20 ቀን 2016ዓ.ም በተካሄደው በዚሁ መርሀግብር ወላጆችና መምህራን ጊዜ ሰጥተው በልጆቻቸው ውጤትና ስነምግባር ላይ በጥልቀት በመወያየት በጋራ ለመስራት ጠንካራ ግንኙነት የፈጠሩበት እንደነበር ከወላጆችና መምህራን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Abune Gorgorios 

 

Abune Gorgorios

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ በ1ኛነት ተሸለመ ፡፡

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በወረዳ 13 ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በወረዳው ከሚገኙ 15 የመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማት መካከል በተደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ ውድድሩን 1ኛ በመውጣት አጠናቋል፡፡

Abune Gorgorios

በ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ታህሳስ 18 ቀን 2015ዓ.ም በወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አዳራሽ ባካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ የሆነው ተማሪ ኪዳነቃል ባያብል በውድድሩ የዋንጫ ፣የሜዳሊያና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆናለች፡፡
ተማሪ ኪዳነቃል ባያብል በቀጣይ በክፍለ ከተማ ደረጃ በሚደረገው ውድድር ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13ን በስሩ የሚገኙ 15 ትምህርት ቤቶችን በመወከል ይወዳደራል፡፡
በዚሁ የጥያቄና መልስ ውድድር በ6ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በተደረገ ወድድር ተማሪ አርሴማ እንዳወቅ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በወረዳ 13 ትምህርት ጽ/ቤት ባዘጋጀው ውድድር ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆናለች፡፡

Abune Gorgorios

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወይራ ቅርንጫፍ የጥያቄና መልስ ውድድር አሸናፊ ሆነ ፡፡

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አዘጋጅነት በ9 የመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማት መካከል በተደረገ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወይራ ቅርንጫፍ ውድድሩን 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በማግኘት አሸናፊ ሆኗል፡፡
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት ታህሳስ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደ የ2016ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪ መክሊት አብይ እና ተማሪ ማርያማዊት አለማየሁ ከ6ኛ ክፍል ሲሳተፉ ተማሪ ያኔት ዓለምነህ እና ተማሪ ሱራፌል አያናው ከ8ኛ ክፍል በውድድሩ ተሳትፈዋል፡፡
በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወይራ ቅርንጫፍ በ9 የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች መካከል በተደረገ በዚሁ የጥያቄና መልስ ውድድር በ6ኛ ክፍል ተማሪ ማርያማዊት 2ኛ በመውጣት የሜዳሊያ ተሸላሚ ስትሆን በ8ኛ ክፍል ተማሪ ሱራፌል 3ኛ በመውጣት ከወረዳው ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል አሸናፊ ሆኗል፡፡

የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

abune Gorgorios

Abune Gorgorios

አዋሬ ቅርንጫፍ በ6ኛና በ8ኛ ክፍል 1ኛ ወጣ ፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 7 ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በወረዳው ከሚገኙ 18 የመንግሥትና የግል ትምህርት ተቋማት መካከል በተደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ 1ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቋል፡፡
በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ታህሳስ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በብሔረ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አዳራሽ በተካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ ተማሪ የሆኑት ተማሪ እስጢፋኖስ ሱራፌል እና ተማሪ ኄራን አለማየሁ በውድድሩ 1ኛ በመውጣት የዋንጫ ፣የሜዳሊያና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

abune Gorgorios

የ6ኛ ክፍሉ ተማሪ እስጢፋኖስ ሱራፌል እና የ8ኛ ክፍሏ ተማሪ ኄራን አለማየሁ በቀጣይ በክፍለ ከተማ ደረጃ በሚደረገው ውድድር የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7ን በመወከል ይወዳደራል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ ተማሪዎች በቀረቡበት ውድድሮች በከፍተኛ ብልጫ በማሸነፍ የሚታወቁ ሲሆን በ2015 ዓ.ም በነበሩ ውድድሮችም በወረዳው በቀዳሚነቱ ይታወቃል፡፡

የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

 

Abune Gorgorios

ሰሚት ቅርንጫፍ በ12ኛ ክፍል ውድድር 1ኛ ሆነ፡፡

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በበሻሌ ጉድኝት በሚገኙ የመንግሥትና የግል ትምህርት ተቋማት መካከል በተደረገ የ12ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድር በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍ ውድድሩን 1ኛ በመውጣት አሸንፏል፡፡
ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በተደረገው የሶሻል ሳይንስ ዲፓርትመንት የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪ አዶናይ ሙልጌታ ሁሉንም የቀረቡለት ጥያቄዎችን በመመለስ በሰፊ ልዩነት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች፡፡

abune Gorgorios

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሻሌ ጉድኝት ስር በሚገኙ 6 የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች መካከል በተደረገው የሶሻል ሳይንስ ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ በመመለስ ተፎካካሪዎቹን በሰፊ ልዩነት በመምራት ተማሪ አዶናይ የወርቅ ዋንጫ እና የወርቅ መዳሊያ ተሸላሚ መሆን ችሏል ።
በሌላ መልኩ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍ በክፍለ ከተማው በቅርቡ በተደረገ የ9ኛ የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪ ምሕረት አስተካከለኝ ውድድሩን በአንደኝነት በመውጣት ማሸነፏአ ይታወሳል፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

Abune Gorgorios

ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ኦንላይን/Online/ ፈተና ተሰጠ ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የ1ኛ መንፈቀ ዓመት አጋማሽ ፈተና በኦንላይ በየቅርንጫፍ ትምህርት ቤታቸው አስፈተኑ፡፡
በአዲስ አበባ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ቅርንጫፍ የአቧሬ፣የለቡ እና የሰሚት ቅርንጫፍ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በ2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና መለማመድ የሚያስችላቸው እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

Abune Gorgorous

ቁጥራቸው 216 የሚሆኑ የአቧሬ ፣የለቡ እና የሰሚት የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ ፈተናው ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ ፈተና መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ ኦንላይ ቢሆን አሁን የወሰዱት ኦንላይን ፈተና ጥሩ ተሞክሮ የሚያገኙበት እንደሚሆን ከተፈታኝ ተማሪዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ይህ የመጀመሪያ መንፈቅ አጋማሽ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚሰጠው ብሄራዊ ፈተና ዝግጅት መነሻ በመሆን በቀጣይ የሚደረጉ ፈተናዎች ለዚሁ ዝግጅት በሚያስችል መልኩ እንደሚሆን ታውቋል፡፡
ከታህሳስ 10 እስከ ታህሳስ 12 ቀን 2016ዓ.ም ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመጀመሪያ አጋማሽ የኦንላይን ፈተና ከተወሰነ የኔትወርክ/Network / መቆራረጥ በስተቀር በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡

Abune Gorgorous

Abune Gorgorios

ለወላጆች፣ለመምህራን እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሥልጠና ተሰጠ፡፡

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ለአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወላጆች ፣ለ12ኛ ክፍል መምህራን እና ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዓለማ ያደረገው የ2016ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎቻችን ውጤታማ ለማድረግ መምኅራን፣ተማሪዎችና ወላጆች ለውጤታማነቱ ያላቸውን ድርሻ ተገንዝበው በጋራ እንዲሰሩ ለማስቻል ያለመ ነው፡፡
ቁጥራቸው ከ200 በላይ የሚሆኑ የለቡ፣የአቧሬ እና የሰሚት ቅርንጫፍ የ2016ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች፣ከ150 በላይ ወላጆች እና ቁጥራቸው ከ30 በላይ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል መምህራን በስልጠናው ተሳትፈዋል፡፡

Abune Gorgorios

ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ስልጠናውን የሰጡት አቶ ዮናስ ግርማ “Techniques of dealing with SAT questions. አቶ ዮሴፍ በቀለ “Motivational Presentation” እና አቶ ወንድዮ ከበደ “Student’s Preparation for National Exam; Managing Possible Test Anxiety of Students, Psychological Readiness, etc.” ስልጠናዎችን ሰጥተዋል፡፡
ለመምህራን እና የትምህርት ኤክስፕርት ባለሙያዎች የተሰጡ ስልጠናውን የሰጡት ዶ/ር ታምሬ አንዱዓለም “Assessing and Evaluating Students Best /How to Prepare Standardized Tests and Assess Students.”፣በ አቶ ዮሴፍ በቀለ “Motivational Presentation” እና አቶ ሽመልስ ገበየሁ “Preparing National Exam taking Students in a fast Track Approach.”ርዕሶች ላይ ስልጠናዎችን ሰጥተዋል፡፡
ሌላው በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አዳራሽ የተሰጠው ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወላጆች ሲሆን በአቶ ዮናስ ተገኝ “How Parents can Manage test Anxiety and Related issue of their Respective Children” እና ”Managing Behaviors of age 17-19 Children towards Realizing Envisaged Goals.” በሚል ርእሰ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ ስልጠና ነው፡፡

Abune Gorgorios

በግራንድ ኤሊያና ሆቴል በተሰጠው የ12ኛ ክፍል መምህራን እና ለትምህርት ዘርፍ ባለሙያዎች ስልጠናን በማስመልከት በሰጡት አስተያየት “ተማሪዎቻችንን በሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት እንዲያስመዘግቡ ምን መስራት አለብን የሚል የማነቃቂያ ስልጠና ነው፡፡ መምህራን መነቃቃት አለብን ይህ መነቃቃት ወደ ተማሪዎችም የሚጋባ በመሆኑ ውጤታማ እንድንሆን ያግዘናል::” በማለት ሀሳባቸውን የሰጡን መምህር ገንዘቤ ገለታው ሲሆኑ” ለመምህራን የሚሰጡ ስልጠናዎች በዚህ መልኩ ሲሆኑ እጅግ በጣም ደስ ይላል፡፡ በቀጣይም ምን መስራት እንዳለብን ያየንበት ስልጠና ነው፡፡ ያሉት መምህር ተመስገን እሸቴ በአቡነ ጎርጎሪዮስ ትምህርት ቤቶች የአቧሬ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የባዮሎጂ መምህር ናቸው፡፡ ሌላኛው ሀሳባቸውን ያጋሩን የሰሚት የእንግሊዘኛ መምህሩ መምህር ተስፋዬ እርገጤ እንደተናገሩት “ስልጠናው እኛ የተማሪዎቻችንን ውጤታመነት ለማረጋገጥ ከዚህ በፊት ከነበሩ ውጤቶች በተሻለ እንዲያመጡ እና ወደፊትም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ምን መስራት እንዳለብን የሚያሳይ ነው” በማለት ገልጸዋል፡፡

Abune Gorgorios

ሌላኛው አስተያየታቸውን የሰጡት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የለቡ ቅርንጫፍ ተማሪ የሆነው ተማሪ አቤል ሚካኤል “…እንዴት ጊዜያችንን መጠቀም እንደምንችል የሚያሳይ ነው፡፡” በማለት ሀሳቡን የሰጠን ሲሆን የአቧሬ ቅርንጫፍ የሆነችው ተማሪ ራኬብ ተመስገን “ስልጠናው አስተማሪና መንፈስን የሚያነቃቃና ለማጥናት የሚያግዘን ነው ብላለች፡፡” የሰሚት ቅርንጫፍ ተማሪ የሆነችው ኤፍራታ ቴዎድሮስም በበኩሏ “በስልጠናው እንዴት አዕምሮአችንን መጠቀም እንደምንችልና ውጤት ላይ መድረስ እንደምንችል የሚያሳይ ነው፡፡” በማለት ሀሳቧን ገልጻለች፡፡

Abune Gorgorios

ስልጠናውን በተመለከተ አስተያየታቸውን የሰጡት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወላጆች በበኩላቸው “ይህንን ስልጠና በማግኘቴ በጣም ዕድለኛ ነኝ፡፡ ብዙ የጎደሉኝ ነገሮች እንዳሉኝ በስልጠናው ያየሁበት ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ስልጠና ቢቀጥል ጥሩ ነው፡፡” በማለት ሀሳባቸውን ያካፈሉን በለቡ ቅርንጫፍ ልጆቻቸውን እያስተማሩ የሚገኙት አቶ አለማየሁ አያሌው ሲሆኑ ሶስት ልጆቻቸውን በአቡነ ጎርጎርዮስ እያስተማሩ የሚገኙት አቶ ዬናስ ታደሰ “ጥሩ ስልጠና ነው፡፡ ያነቃቃል ለልጆቻችን ጥሩ ድጋፍ እንድናደርግ የሚያደርግ ነው፡፡ በዚህ ቢቀጥል መልካም ነው፡፡” ያሉ ሲሆን እኛና ልጆቻችን ምን ያህል ተራርቀን እንዳለን የሚያሳይ ነው፡፡ልጆቻችንን እንዴት አድርገን መያዝ እንዳለብን የሚያሳይ ነው፡፡የተሻለ ውጤት እንድናመጣ የሚያስችል ስልጠና ነው፡፡” በማለት ሀሳባቸውን የሰጡን የሰሚት ቅርንጫፍ የወላጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሰፍነ ተረፈ ናቸው፡፡ይንን መሰል ስልጠናዎች አነቃቂና መነሳሳትን እንደፈጠረባቸው ከተሳታፊዎች ለምዳት ተችሏል፡፡

Abune Gorgorios

Esdros Construction

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እሑድ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም አካሂዷል፡፡

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ንዱስትሪ አ.ማ የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር መሀሪ መኮንን አክሲዮን ማኅበሩ በ2015 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን አበይት ጉዳዮች በሪፖርታቸው ሲገልጹ፤
1. በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተሞች 27 ቅርንጫፍ የአቡነ ጎርጎሪዮስ ትምህርት ቤቶች 19,014 ተማሪዎችን እያስተማረ መሆኑን፤
2. በአዲስ አበባ ከተማ 22 አካባቢ እያስገነባ ያለው ባለ 15 ወለል ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የመኖሪያ ቤት (አፓርታማ) ግንባታው 45 በመቶ መድረሱን፤
3. የ አክሲዮን ማህበሩ ዓባላት 3,585 መድረሱን እንዲሁም ኩባንያው በአሁኑ ወቅት 160 ሺህ አክሲዮን ለመሸጥ እየሰራ መሆኑን፤
4. ኩባንያው ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲኖር ለማድረግ በተለይም የባለአክሲዮኖች አክሲዮን አስተዳደር መተግበሪያ (Application) አልምቶ ተግባራዊ ያደረገ መሆኑን እንዲሁም፤
5. አክሲዮን ማህበሩ በ 2015 በጀት ዓመት የነበረውን ጥቅል የፋናንስ ሪፖርት በማቅረብ በጉባኤው እንዲፀድቅ አድርገዋል፡፡

ከዚህም ሌላ ጉባኤው
 የውጭ ኦዲተር ሪፖርት በመስማት አጽድቋል፣
 የዲሬክተሮች ቦርድ የ2016 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ለጉባኤው ቀርቦ ፀድቋዋል፣
 የ2015 በጀት ዓመት የትርፍ ክፍፍል ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ተሰጥቷል፣
 ተተኪ የዲሬክተሮች ቦርድ አባልን መርጧል ፣የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት አበል በመወሰን ስብሰባውን አጠቃሏል፡፡

 

Esdros Construction

Abune Gorgorios

ከፍለው መማር ለማይችሉ ተማሪዎች ነጻ የትምህርት እድል ተሰጠ፡፡

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች የትምህርት ዘመኑን የትምህርት ክፍያ ከፍለው መማር ላልቻሉ 73 ተማሪዎች የነጻ ትምህርት እድል ሰጠ፡፡

ቁጥራቸው 73 የሆኑ ተማሪዎች በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወላጆቻቸው በተለያየ ምክንያት የትምህርት ክፍያን ለመፈጸም በመቸገራቸው የተሰጠ የነጻ የትምህርት እድል መሆኑን ለማወቅ የተችሏል፡፡
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየሠራ የሚገኝ ሲሆን በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወላጆች ላይ በሚገጥም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመፍታት ልጆቻቸው ተረጋግተው እና ውጤታማ ሆነው እንዲማሩ እየሠራ ይገኛል፡፡
እነዚህም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በ15 ቅርንጫፍ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል ሲሆኑ በ2015ዓ.ም ለ50 ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል የተሰጠ ሲሆን በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን 23 ተጨማሪ አዳዲስ ተማሪዎችን በመጨመር ቁጥሩ 73 እንደደረሰ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኩባንያው ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ነጻ የትምህርት ዕድል የሰጣቸውን 73 ተማሪዎችን የብር 1.3 ሚለዮን ብር የሸፈነ ሲሆን በአራዳ እና ቃሊቲ ክፍለ ከተማም ለሚገኙ አረጋውያን ድጋፍ የሚሆን ከ200 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡

 

Abune Gorgorios

Abune Gorgorios

የተማሪዎችን ዕለታዊ ጉዳይ መረጃ የሚሰጥ መተግበሪያ ሥራ ጀመረ፡፡

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን የየዕለት ጉዳዮች መረጃ የሚሰጥ መተግበሪያ ሥራ መጀመሩን የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክፍል አስታወቀ፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክፍል ያዘጋጀው ይኸው መተግበሪያ ወላጆች ስለ ልጆቻቸው የትምህርት ቤት ውሎ/ሁኔታ እና የትምህርት ጉዳዮችን ለመከታተል የሚያስችል መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡
መተግበሪያው ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት ውጤት ት/ቤት መምጣት ሳይጠበቅባቸው ማየት እንዲችሉ ከማድረጉም ባሻገር ልጆቻቸው በየዕለቱ ትምህርት ቤት መገኘታቸውን እና ወሳኝ የሆኑ የቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱን መረጃዎች ማግኘት የሚያስችላቸው ሆኖ መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡
ወላጆች በስልካቸው ላይ መተግበሪያውን በማውረድ እና በመጠቀም ብቻ የልጆቻቸውን ዕለታዊ መረጃ ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

 

Abune Gorgorios